Kingdom Revival
  • Home
  • Voice

Voice

ቅዱሳን እርስ በርስ የምንተናነፅበት ይሁንልን! 

ከሰፈር ውጡ 2

6/5/2020

0 Comments

 
ዳንኤል ሚዛን
                     ሰላም ለኲልክሙ  !
              ከሰፈር ውጡ !!!
ካለፈው የቀጠለ......
“እንግዲህ ነቀፌታውን እየተሸከምን ወደ እርሱ ወደ ሰፈሩ ውጭ እንውጣ፤”
         ዕብራውያን 13፥13
​፨  ክርስትና በሰማይ የክርስቶስን ስፍራ ካሰጠን በምድር ላይም እንዲሁ የክርስቶስን ስፍራ ይሰጠናል ።
፨   በሰማይ ያለው የክርስቶስ ባለጠግነት በምድር ላይ ያለውን የክርስቶስን ነቀፋ ይጠይቃል ።
፨   በላይ በሰማይ በመጋረጃው ውስጥ ከክርስቶስ ጋር ያለው ስፍራ በዚህ በታች በምድር ከክርስቶስ ጋር በውጭ መሆንን ያስከትላል ።

፨  ክርስትና ለአማኝ በሰማይ ታላቅ ስፍራን ያሰጣል ነገር ግን በምድር ላይ ከነቀፋ በስተቀር ምንም ቦታ አያሰጠውም ።

      በዘሌዋውያን አራት ላይ በዝርዝር እንደተገለፀው ለኃጥያት መሥዋዕት የሚቀርበውና ከሰፈር ውጭ የሚቃጠለው ሥጋ ኃጥያትን በተመለከተ የእግዚአብሔርን የተቀደሰ ፍርድ ያሳያል ።
፨  ክርሰቶስ በደሙ ሕዝቡን ይቀድስ ዘንድ ከሰፈር ውጭ ወይም ቃሉ እንደሚለው ከበር ውጭ መከራን ተቀበለ፤ ምክንያቱም ደግሞ እኛ በመጋረጃው ውስጥ የከበረ ስፍራ ይኖረን ዘንድ እርሱ በእኛ የፍርድ ቦታ ከሰፈር ውጭ መገኘት ነበረበት ።

፨  ከኃጥያት ተለይተን ለእግዚአብሔር ደስታና  ምስጋና እንድንሆን አስቀድሞ ኃጥያታችን በእኛ ላይ የሚያመጣውን ፍርድ ተሸካሚ ማግኘት ነበረበት ።
፨  በዘመናት ሁሉ ለእግዚአብሔር የፀጋ ክብር መመስገኛ የሚሆን ሕዝብ በመጋረጃው ውስጥ ይኖራል፤ ምክንያቱም ደግሞ አንድ ጊዜ ኢየሱስ ባለፉት ዘመናት ከሰፈር ውጭ ወደ መተው ሄዷልና ነው።

       ፨  ስለዚህ አሁን ተግባራዊ  የሆነውን ምክር እንመልከት፡
ይህ ከሰፈር ውጭ የተባለው ስፍራ ከእግዚአብሔር የሚመጣ ፍርድ የመቀበያ ስፍራ መሆኑ አብቅቶ ከሰው ነቀፋ የምንቀበልበት ስፍራ ነው።
         ከእግዚአብሔር ፍርድ ለመቀበል ወደ ውጭ አልተጠራንም፤ ወደ ውጭው እንድንወጣ የተጠራነው በሚቻለን ሁሉ የክርስቶስ በሆነ ነገር በሰዎች እየተነቀፍን ልንኖር ነው።
፨  ኢየሱስ ስለኃጥያታችን ከእግዚአብሔር የተቀበለልንን መከራ( ፍርድ )  ልንጋራው አንችልም፤  ነገር ግን ከሰው የተቀበለውን ስድብና ነቀፋ እንጋራዋለን ወይም  መጋራት አለብን ፤ እርሱ ፍርዳችንን ሊቀበል ከሰፈር ውጭ ወጣ ፤ እኛ ደግሞ የእርሱን ነቀፋና ስድብ ልንሸከም ከሰፈር ውጭ እንወጣለን ።

፨  እግዚአብሔርን በሚጠላ ሕዝብ መካከል ጌታ ኢየሱስ ለእግዚአብሔር ቀናተኛ ነበር፤ ከዚህም የተነሳ እንደ እንግዳና እንደ ሌላ ተቆጠረ፤ ቅናት ወደ ውጭው የነቀፋ ቦታ ወሰደው።
      እግዚአብሔርን በምትጠላ አልያም በማትፈልግ ዓለም ውስጥ ከእግዚአብሔር የተላከ ሆኖ ተገኘ ። በምድር ላይ በሰዎች መካከል መገኘቱ ሰዎች በእግዚአብሔር ላይ ያላቸውን ጥላቻ የሚገልጡበትን ዕድል ሰጣቸው። ስለሆነም በእግዚአብሔርን ላይ የነበራቸውን ጥላቻ በክርስቶስ ላይ ተወጡ ።

“የቤትህ ቅንዓት በልታኛለችና፥ የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆአልና።” 
                       መዝሙር 69፥9

እንዳለ እንዲሁም ፡ በመዝ 69÷7 ላይ፡ ጌታም ስለ አንተ ስድብን ታግሻለሁና ብሏል ።
፨  ክርስቲያን የተጠራው ሰዎች ለክርስቶስ የሰጡትን ቦታ ተቀብሎ በዕብራውያን 13÷13 ላይ " ሰፈር " ከተባለውና ለፍጥረታዊው ሰው ማራኪነት ካለው ሥርዓተ ኃይማኖት እና የሃይማኖት ድርጅቶች እሳቤ ወደ ውጭ እንዲወጣ ነው ።
         
፨  በተጨማሪም ክርስትና በንፁሕ ህሊና ወደ እግዚአብሔር መቅረብን ያጎናፅፋል። ክርስትና ከፍጥረታዊ ሰው በጎ ኅሊናን በመፈለግ ፈንታ ሙሉ በሙሉ በሥጋ የሆነውን ሰው ታስወግዳለች። ስለዚህም ክርስቶስን ባልተቀበለች ዓለም ውስጥ የክርስቶስን ነቀፋ ይዛለች ።

    ..... ይቀጥላል .....
              አቤቱ
²⁰ በዘላለም ኪዳን ደም ለበጎች ትልቅ እረኛ የሆነውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ያወጣው የሰላም አምላክ፥
²¹ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን በእናንተ እያደረገ፥ ፈቃዱን ታደርጉ ዘንድ በመልካም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ያድርጋችሁ፤ ለእርሱ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።

             ወንድም ዳንኤል ሚዛን
0 Comments



Leave a Reply.

    የቅዱሳን ድምፅ ​

    ክብር ይሁንለት!

    Picture

    Archives

    September 2020
    July 2020
    June 2020
    May 2020

    Categories

    All

    RSS Feed

Come, let us worship Him
Psalm 95:6 NCV
  • Home
  • Voice