Kingdom Revival
  • Home
  • Voice

Voice

ቅዱሳን እርስ በርስ የምንተናነፅበት ይሁንልን! 

እንዴት ይታወቃል?

5/22/2020

0 Comments

 
 ሰላማዊት እሸቴ 

​እንዴት ይታወቃል ዓማኝ መሆኔ 
የመንፈሱ ፍሬዎች ካልታዩ በህይወቴ
የበደሉኝን ሰዎች ይቅር ማለት ካልቻልኩ
ከሃሜት ጥላቻ ከበቀል ካልራቅሁ
ውሸት መናገር ቀሎ ከታየኝ
ዓጠገቤ ያለውን ሰው መውደድ ሲከብደኝ
በሌሎች ስኬት ላይ መደሰት ከዓቃተኝ
እንዴት ይታወቃል ዓማኝ እንደሆንኩኝ
እግዚአብሔርን መፍራት ከሌለ በልቤ
በሌላው ሰው ብቻ መፍረድ ከሆነ ልማዴ
የራሴን ትልቅ ግንድ ሳላወጣ ከአይኔ
በባልንጀራዬ በሐሰት ከመሰከርኩ
የተቸገረውን ወገኔን ካላሰብኩ
ለራሴዉ ጠግቤ ብቻ ካደርኩኝ 
እምነቴ በስራ ካልተገለፀማ ምኑን ዓማኝ ሆንኩኝ
ቅጥ ያጣ ዓለባበስ ሆን ብዬ ለብሼ
ሰው እንዲሰናከል ምክንያት ቀይሼ
ታማኝነት ጎድሎኝ ለመስረቅ ከዳዳሁ
በዓይን ዓምሮት ሩጫ ሽምጥ ከጋለብኩ
ለቅዱስ ትዳሬ ለእግዚአብሔር ካልታመንኩ
መብቴን ተጠቅሜ አምላኬን ካሳዘንኩ
የባልንጀራዬን ቤት ሃብት ከተመኘው 
የእኔ ዓማኝነት እኮ ምኑ ላይ ነው
ለእናት ለዓባቶቼ ዓክብሮት ከሌለኝ
በእሽታ መንፈስ መታዘዝ ክዓቃተኝ
የዓደባባይ ህይወቴ በጓዳዬ ካልታዬ
ምን ትርጉም ይሰጣል ታዲያ ክርስትናዬ
የክፋት ስር ለሆነው ለገንዘብ ፍቅር
ከተገዛሁለት እኩል ከእግዚአብሔር
በትሕትና መኖር ሞኝነት ከመሰለኝ
በትዕቢት ተሞልቼ ውድቄቴ ከተረሳኝ
በወንድማማቾች መካከል ጠብን ከዘራሁ
እግዚአብሔር በዓምሳሉ ለፈጠረው ሰው ሞት ከተመኘሁ
ዓማኝ ነኝ ማለቴ ትርጉሙ የቱጋ ነው 
የህይወት መውጫ የሆንውን ልቤን ካልጠበቅሁ
ዓንደበቴን ሳልገታ ሰውን ከዘለፍኩ
ወገኔ እንዳይሮጥ መረብ ከዘረጋው
ተጠልፎ ሲወድቅ እኔ ጥዬው ላልፈው
እንደዚህ ካሰብኩኝ የእውነት ዓማኝ ነኝ ?
ልብን የሚያይ ጌታ ራሴን ቢያሳየኝ
ዓማኝ መባሌ እሺ ምኑ ላይ ነው
ዓማኝ ማለት ህይወት ለእውነት መኖር ነው
ብትወድዱኝ ትዕዛዜን ጠብቁ ብሎዓልና ጌታ
መታዘዝ በመውደድ መውደድም በመታዘዝ ይታሰራሉና
ይገለፃሉና ይታወቃሉና።
0 Comments



Leave a Reply.

    የቅዱሳን ድምፅ ​

    ክብር ይሁንለት!

    Picture

    Archives

    September 2020
    July 2020
    June 2020
    May 2020

    Categories

    All

    RSS Feed

Come, let us worship Him
Psalm 95:6 NCV
  • Home
  • Voice