ዳንኤል ሚዛን
ሰላም ለኲልክሙ ! ከሰፈር ውጡ !!! “እንግዲህ ነቀፌታውን እየተሸከምን ወደ እርሱ ወደ ሰፈሩ ውጭ እንውጣ፤” ዕብራውያን 13፥13 ፨ የውጭው ስፍራ ብዙ መብቶች የሌሉትና በሰፈር ውስጥ በነገሮች ስርዓት ባሉት ዘንድ በሙላት የማይቻል የመፅሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች ተግባራዊ የሚሆኑበት ስፍራ ነው ።
0 Comments
ሰላማዊት እሸቴ
እንዴት ይታወቃል ዓማኝ መሆኔ የመንፈሱ ፍሬዎች ካልታዩ በህይወቴ የበደሉኝን ሰዎች ይቅር ማለት ካልቻልኩ ከሃሜት ጥላቻ ከበቀል ካልራቅሁ ውሸት መናገር ቀሎ ከታየኝ ዓጠገቤ ያለውን ሰው መውደድ ሲከብደኝ በሌሎች ስኬት ላይ መደሰት ከዓቃተኝ እንዴት ይታወቃል ዓማኝ እንደሆንኩኝ ኤፍሬም ወሰኑ
የተማረ ሲያስተምር ትምህርቱን ሕይወት ይሰጠዋል፤ እንዲሁም የአመነ አሳማኝ ለእምነቱ ሕይወት ሰለሚሰጠው ለአማኙ ሕይወት እና ጉልበት ይሆንለታል፥እውቀትንም ሆነ እምነትንለማስተላለፍ ደግሞ ኃይልን ይጠይቃል ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደቀ መዝሙርቱ ሕይወት ያደረገው ይህን ነው።በጨለማ ላለው የሰው ፍጥረት በክፉ ዓለም ከተያዘው ልብ የተነሳ ለማያምንትውልድ እውነት እና ሕይወት የሆነውን ኢየሱስን መስክረው እንዲታመኑ መጀመርያ ያደረገው እነሱ እንዲያምኑ ማድረግ ነው። ሚኪያስ አበበ Drift
Uncovered my sin exposed wide open Ashamed my goodness are filthy rags In the moment t’was grace that found my home ሰላማዊት እሸቴ
የቀናት ፈጣሪ ቢጠይቀን ጊዜን እራሱ የሰጠንን ሊነግረን ሊያሳየን ቢፈልግ በቃሉ የሚፀየፈውን ተገኝ በጓዳህ ተውና መባከን አንብብ ቅዱስ ቃሌን በአገልግሎት ስም ብዙ ወጣህ ወረድክ ሳትሰጠኝ ልብህን ባልንግጀራህን እንደ ራስህ ውደድ ያልኩትን አቃለህ በአንፃሩ ጥላቻ ቅናት ሃሜት ቂምን በሙሉ ተሞልተህ አመልክሃለው አትበል በደም የረከሱ እጆችህን አንስተህ |